የአዋሽ መልካሣ ዕድገት ማህበር
Awash Melkassa Development Association
ውድ የአዋሽ መልካሣ የአሁንና የቀድሞ ተማሪዎች፦
እኛ ቀደም ብሎ የአዋሽ መልካሣ ነዋሪዎች የነበርን አሁን ግን በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ሰዎች ያሳደገንንና ዛሬ ላለንበት ኑሮ እንድንበቃ የረዳንን ማህበረሰብ ለመርዳት በመነሳሳት አንድ መህበር አቋቁመናል። የማህበሩንም ስም የአዋሽ መልካሣ ዕድገት ማህበር (Awash Melkassa development Association) ብለን ሰይመነዋል።
ይኽ ማህበር ዓላማ አድርጎ የተነሳው በመጀመሪያ በዉጭ ሃገር ያሉ ዲያስፖራዎች የቀድሞ ፍቅራችንን በመጠበቅ በሃሳብና በተለያየ መንገድ በመረዳዳት አባቶቻችን ለእኛ፤ እኛም ለልጆቻችን፤ ልጆቻችንም ለልጆቻቸው፤ በኛ ዉስጥ የሰረጸውን ፍቅር ለትውልድ እንዲያሻግሩና ያን ያደግንበትን ፍቅር ለዘለቄታ ለማቆየት እንድንችል ነው። ሁለተኛው ደግሞ የአዋሽ መልካሣን ህብረተሰብ በተለይም በትምህርት ቤት ያለውን ትውልድ ለማምበረታታትና ሞራላቸው ከፍ ያለ ትውልድ በመፍጠር ያንን ህብረተሰብ በመተሳሰብና በፍቅር እንዲሁም አቅማችን በፈቀደው መጠን ለማሳደግ ነው።
ይኽንን መሕበር ለመፍጠር አስራ አምስት ያህል መስራች አባላት ላንድ ዓመት ያህል ያለማቋረጥ በየሳምንት በzoom communication ዓማካይነት በመገናኘት ማህበራዊ መዋቅሩን በማበጀትና የመተዳደሪያ ደንቦችን በማዘጋጀት እንዲሁም ህጋዊና ዕውቅና ያለው ማህበር ለመፍጠር ችለናል።
የፊታችን September 5, 2022 7:00pm በዋሺንግተን ዲሲ አቆጣጠር በ zoom ዓማካይነት በምናደርገው የመጀመሪያው ምዕራፍ የምስረታ ስነስራዓት ላይ እንዲገኙልን ለአዋሽ መልካሣ የሰሜን አሜሪካ ዳያስፖራ አባላት ሁሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
Zoom ID: 4598613262
Pass word: to be provided
ሲሆን (የ ፓስዎርዱ ፊደላት በ ካፒታል ፊደል መሆኑን አይዘንጉ)
እግዚአብሄር እንዲሁ በፍቅራችን ጠብቆ ያቆየን!!
እናመሰግናለን
ተሾመ ዋኬኔ
የመስራች ኮሚቴው ሊቀመንበር
Input your search keywords and press Enter.